የቀን ገቢ ግምት ግብር ስሌት

Posted in Know How

በአዲስ አበባ ከተማ የ2009 ዓ.ም. አማካይ የቀን ገቢ ግምት መሰራቱን ተከትሎ የግምቱ ውጤት ለግብር ከፋዮች መገለፅ ተጀምሯል፡፡ የግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምት እና ዓመታዊ የሽያጭ መጠናቸው እንዲሁም ዓመታዊ ሽያጫቸውን መሰረት አድርጎ የግብር ከፋዮች ደረጃ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የተገለፀውን መረጃ ማለትም የቀን ገቢ ግምቱንና ዓመታዊ የሽያጭ መጠኑን በማየት ብቻ ያን ያህል ግብር ክፈሉ እንደተባሉ ቆጥረው የመደናገጥና የማማረር ሁኔታዎች መስተዋላቸውን ተከትሎ የግብር ከፋዮች ዓመታዊ የቀን ገቢ ግምቱንና ዓመታዊ ሽያጩን መሰረት አድርጎ ገቢ ግብር እንዴት እንደሚሰላ ከዚህ ቀጥሎ በምሳሌ እናቀርባለን፡፡


ምሳሌ 1፡- በርበሬ ቅመማ ቅመም ንግድ
የቀን ገቢ ግምት መጠን፡- ብር 1,500
ብር 1500 * በ365 ቀናት = ብር 547,500 /ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ/
የዘርፉ ትርፍ መተመኛ 10% = 547,500
ግብር የሚከፈልበት ገቢ = 54,750
ግብር መጣኔ 20% = 10,950
ተቀናሽ - 3,630
ተከፋይ ግብር = 7,320


ምሳሌ 2፡- የባህል ዕቃዎች
የቀን ገቢ ግምት መጠን፡- ብር 2000
ብር 2000 * በ300 ቀናት = ብር 600,000 /ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ/
የዘርፉ ትርፍ መተመኛ 14% = 600,000*14% = 84,000
ግብር የሚከፈልበት ገቢ = 84,000
ግብር መጣኔ 25% = 84,000 * 25% = 21,000
ተቀናሽ = 6780
ተከፋይ ግብር = 14,220


ምሳሌ 3፡- ፀጉር ቤት
የቀን ገቢ ግምት መጠን = ብር 2,800
ብር 2,800 * በ365 ቀናት = ብር 1,022,000 /ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ/
ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ብር = 1,022000
የዘርፉ ትርፍ መተመኛ 10% = - 102,200
ጠቅላላ ወጪ = 919,800
ጠቅላላ ግብር የሚከፈልበት ገቢ = 102,200
ግብር ምጣኔ 30% = 30,660
ተቀናሽ - 11,460
ተከፋይ ግብር = 19,200


ማሳሰቢያ፡- ከምሳሌው እንደምንረዳው ግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምቱን ተከትሎ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ዓመታዊ ግብር እንደሚባለው በአብዛኛዎቹ ላይ የተጋነነ አይደለም፡፡ የተመደበላቸው ግብር አንድ ተቀጣሪ ከደመወዙ ላይ ከሚከፍለው ግብር አነስተኛ ነው፡፡ ከላይ የተገለጹት ምሰሰሌዎች ለደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- የ10ሺ ብር ደመወዝተኛ በወር 2ሺ 45 ብር፤ በዓመት ከሚከፈለው 120ሺ ብር ደግሞ 24ሺ 540 ብር ግብር ይከፍላል፡፡ 120ሺ ብር ዓመታዊ ገቢ ያለው ነጋዴ ግን የትርፍ መተመኛ መቶኛው 10 በመቶ ላይ ካረፈ ግብር የሚጠየቅበት ገቢው 10 በመቶ ወይም 12ሺ ብር ይሆናል፡፡ ቀሪው 90 በመቶ ወይም 108ሺ ብር እንደ ወጪ ይታይለትና ከግብር ውጪ ይሆናል፡፡ 12ሺውን ደግሞ በግብር ማስከፈያ መጣኔ ሲሰላለት 10 በመቶ ላይ ያርፍና 1ሺ 200 ብር ብቻ ዓመታዊ ግብር ይጠየቃል፡፡ ስለዚህ የነጋዴውን 1ሺ 200 ብር ከደመወዝተኛው 24ሺ 540 ጋር ማነጻጸር በቂ ነው፡፡

Visitors: Yesterday 3 | This week 0 | This month 591 | Total 424264

We have 516 guests and no members online