ለጌድዮ ተፈናቃዮች ከሃያ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብሃዊ ድጋፍ ተደረገ

Posted in Latest News


  (የገቢዎች ሚኒስቴር፣ መጋቢት 8/2011 ዓ.ም)
  የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ በመሆን    ለጌድዮ ተፈናቃዮች 21,700,000 ብር የሚገመት ስኳር፣ የምግብ ዘይትና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት(መጋቢት 8/2011 ዓ.ም) በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ ጌድዮ ዞን ከሀዋሳ 170 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ገደብ ወረዳ እና ከገደብ 25 ኪ.ሜ ገባ ብሎ የሚገኘው ጎቲቲ በመገኘት ተፈናቃዮችን በመጎብኘት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተፈናቃዮቹን በጎብኝቱ ወቅት “ህመማችሁ፣ መንገላታታችሁ እና ጉስቁልናችሁ የእኛ የእያንዳንዳችን ችግር እንደሆነ ይሰማናል” ብለዋል፡፡
“ወደ ቀድሞ መኖሪያችሁ በመመለስ በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ሁሉ ከጎናችሁ አለን” ብለዋል፡፡ “የሰላም እጦት ምን ያህል ለችግር እንደሚዳርግ አይታችሁታልና ወደ ቀድሞ መኖሪያችሁ ስትመለሱ የሰላም አምባሳደር እንድትሆኑ” በማለት ለተፈናቃዮቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ባሳላፍነው የክረምት ወቅት ለጌድዮ ተፈናቃዮች ሚኒስቴሩና ኮሚሸኑ 84,420, 000 ብር የሚገመት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት ብቻ በድምሩ 106 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡

Visitors: Yesterday 43 | This week 88 | This month 779 | Total 434506

We have 188 guests and no members online