ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀሙን መገምገም ጀመረ

Posted in Latest News

 

 

 

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ሃላፊዎች በተገኙበት፣በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዉ የሚገኙ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቅ/ጽ/ቤቶች ስራ አስኪያጆች እና የተወሰኑ የዋናዉ መስሪያ ቤት ዳይሬክተሮች ተሳታፊ በሆኑበት የመስሪያ ቤቱን የ 7 ቀናት የስራ እንቅስቃሴ ግምገማ ዛሬ ጥቅምት 25/2011 ዓ.ም በዋናዉ መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ገመገሙ፡፡
ባለፈዉ ሳምንት ማለትም ጥቅምት 21/2011 ዓ.ም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቢሾፍቱ ከተማ ባካሄደዉ ግምገማ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ100 ቀናት ዉስጥ 77 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ አዉጥቶ ይህንን የገቢ ዕቅድ ዘርፎችና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወደ ራሳቸዉ ወስደዉ ከራሳቸዉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የየራሳቸዉን ዕቅድ አዉጥተዉ ያወጡትን ዕቅድ ለሰራተኞቻቸዉ እንዲያወያዩ አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር ፡፡
የስራ ክፍሎቹ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት መፈጸማቸዉን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዉ ግምገማ የተካሄዶበት ለእቅዱ የማዳበሪያ ሃሳቦች የተሰጠበት ሲሆን በቀጣይም የታቀደዉን የ 100 ቀናት የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ስራዎችን በስራ ክፍል
ደረጃ በየቀኑ፣የስራ ሰዓት በማይጋፋ መንገድ በማወያየት፣በማኔጅመንት ደረጃ ደግሞ በየሳምንቱ እየገመገመ የተሻለ አፈጻጸም ያሳየዉን ሰራተኛ እና የስራ ክፍል በማበረታታት ያልሰራዉን ደግሞ ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ በየደረጃዉ ተጠያቂ እንዲሆን በማድረግ የገቢ ዕቅዱን ለማሳካት በጊዜ የለንም መንፈስ መንቀሳቀስ እንደሚገባ በዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳስበዉ እንደ ዛሬዉ አይነት ዉይይቶች በተመሳሳይ ከስራ ሰዓት ዉጪ ቅዳሜ ከሰዓት ወይምእሁድቀን እየተገናኙ የመገምገም ባህላችን በፕሮግራም ተይዞ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል፡፡

 

Visitors: Yesterday 43 | This week 87 | This month 778 | Total 434505

We have 408 guests and no members online