የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት የስምምነት ሰነድ ተፈረመ

Posted in Latest News

የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት የስምምነት ሰነድ ተፈረመ
(የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ሚያዝያ 15/2011 ዓ.ም)

ኮንትሮባንድ የሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ የህዝብ ጤናና ደህነት እና ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከል የጉምሩክ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል፡፡
የስምምነት ሰነዱን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ ተፈርሟል፡፡

ወቅቱ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ፤ ስምምነቱ ባለፉት ዓመታት የጉምሩክ ኮሚሽንና የፀጥታ አካላት በየራሳቸው ሲንቀሳቀሱ የነበረው በማቀናጀት ኮንትሮባንድን ለመከላከል የበለጠ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም የሁለቱ ተቋማት በጋራ ከመስራት በተጨማሪ የተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

በጉምሩክ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ቀደም ሲል ሌሎች ስራዎችን ደርቦ ሲሰራ የነበረው የፀጥታ መዋቅር በአሁኑ ወቅት ኮንትሮባንድ መከላከል ዋነኛ ስራው የሆነ የጉምሩክ ፖሊስ ተደራጅቷል፡፡
የጉምሩክ ፖሊስ አደረጃጀቱ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሆኖ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ የስራ ስምሪት የመስጠትና ስራውን በጋራ የመገምገም አሰራር ይከተላል፡፡
በአሁኑ ወቅት በጥናት ላይ በመመስረት 50 በመቶ በሚሆኑት የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የጉምረክ ፖሊስ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በቀሪዎቹ ኬላዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ሪፎርም ከጀመረ ወዲህ 1.3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር እንዳዋለ የሚታወስ ነው፡፡

Visitors: Yesterday 51 | This week 69 | This month 365 | Total 431219

We have 236 guests and no members online