ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ተያዘ

Posted in Latest News

   

በቶጎ ጫሌ የጉምሩክ ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ጨምሮ የ3 ሀገራት ገንዘብ በጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ሚያዚያ 7/2011 ዓ.ም
ገቢዎች ሚኒስቴር

በዛሬዉ ዕለት ኮድ 3 -04867 ድሬ የሆነ ተሽከርካሪ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ በቶጎ ጫሌ ኬላ 182247 የአሜሪካን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር 5285163/አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ አንድ መቶ ስልሳ ሶስት/ብር፡110920 /አንድ መቶአስር ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ/የዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ገንዘብ በእለቱ ምንዛሬ ዋጋ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር 887360/ስምንት መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺ ሶስት መቶ ስልሳ/ብር፡የሳዲ ሪያድ 235375/ሁለት መቶሰላሳ አምስት ሺ ሶስት መቶ ሰባ አምስት በእለቱ ምንዛሬ ዋጋ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር 1835925/አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሰላሳ አምስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት ብርበቀን 6/2011 ዓ.ም በቶጎ ጫሌ ጉሙሩክ ኬላ በጉሙሩክ ፍተሸ ሰራተኞች አብዱርሃማን ቃሲም አደን እና አብዱልቃድር አብዱላሂ አናን ከተባሉ ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡የግል ጥቅማቸዉ ሳያስቀድሙ እና የኮንትሮባድስቶች ድለላ ሳይበግራቸዉ ለሀገራቸው ሌት ተቀን እየሰሩ ለሚገኙት የቶጎጫሌ ጉሙሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች የገቢዎች ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከፍ ያለ አድናቆታቸውን እና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ከዚህ ቀደምም በቶጎጫሌ ኬላ በርካታ ቁጥር ያለው የውጭ ሀገር ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

Visitors: Yesterday 1 | This week 31 | This month 537 | Total 430124

We have 635 guests and no members online