በያዝነው ሳምንት 4.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

Posted in Latest News

    

በያዝነው ሳምንት 4.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

(መጋቢት11/2011 ዓ.ም)                

በያዝነው ሳምንት በተለያዩ የመቆጣጠሪያ ጣቢዎች በድምሩ 4,480,305 ብር የሚገመት የኮንትሮባድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ቡሌ ሆራ የመቆጣሪያ ጣቢያ ላይ 627,100 ብር የሚገመት ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ቻርጀሮች እና ጀነሬተሮች የሚያካትት የኮንትሮባንድ ዕቃ መጋቢት 9/2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ3-94467 አ.አ በሆነ ጸሸከርካሪ ሲጓጓዝ በኦሮሚያ ፖሊስና በጉምሩክ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ3-19171አ.አ FSRተሸከርካሪ 697,300 ብር ግምታዊ ዋጋው ኮንትሮባንድ የሆነ ኤሌክትሮኒክስ፣ መለዋወጫ እና ፌሮ ብረት በኦሮሚያ አድማ ብተና ፖሊስ፣ በመከላከያ ሰራዊት እና በጉምሩክ ሰራተኞች መጋቢት 9/2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሏል

ግምታዊ ዋጋ 1200000 ብር የሆነ መድሃኒት፣ አልባሳት፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፣ ስኳር እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 5፡00 ላይ የሰሌዳ ቁጥር 01526 ሱማ እና 02621 ሱማ በሆኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ጅግጅጋ ለማስገባት ሲሞከር በአድማ ብተና አባላት እና በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል፡፡

በደቡብ ክልል ገደብ ፣ ወናጎ እና አርባ ምንጭ ከተሞች 2,026,105 ብር የሚገመት መድሃኒት፣ አልባሳት እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

Visitors: Yesterday 43 | This week 88 | This month 779 | Total 434506

We have 139 guests and no members online