በአምስት ወራት ብቻ ከ9.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች ተከፋፍሏል

Nested Applications

Asset Publisher

Asset Publisher

Asset Publisher

null በአምስት ወራት ብቻ ከ9.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች ተከፋፍሏል

በአዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ስርዓት በአምስት ወራት ብቻ 9.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች ተከፋፍሏል

ታህሳስ 13/2013 .

የገቢዎች ሚኒስቴር አዲሱን የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በተያዘው 2013 በጀት ዓመት ተግባራዊ መደረጉን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ማጣጣምና የክልሎች ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ሀሶ በመግለጫው ወቅት እንደገለፁት 2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ተርንኦቨር ታክስ እና ኤክሳይዝ ታክስ በድምሩ 9.87 ቢሊዮን ብር ገቢ ለክልሎች ተላልፏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 8.7 ቢሊዮን ብር ዕድገት አሳይቷል፡፡

አዲሱ የጋራ ገቢ ማከፋፈያ ቀመር ስርዓት ተግበራዊ መሆን የክልሎችን የመልማት አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያጎለብት እና የክልሎችን አቅም ከማጠናከር አንፃር ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው አቶ መሀመድ ገልጸዋል፡፡

የክልሎች የጋራ ገቢን በተመለከተ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 98 መሰረት በሁለቱ /ቤቶች 2/3 ድምፅ ተደንግጎ የነበረ ቢሆንም ትግበራው አዳጋች በመሆኑ የህዝብ ተወካዮች /ቤት መጋቢት 30 1989 . ባካሄደው 2 ዓመት የስራ ዘመን 38 መደበኛ ስብሰባ አንቀፁን በማሻሻል በጋራ እንዲጣሉና እንዲሰበሰቡ ከተደነገጉ የታክስ ምንጮች ላይ ታክስ የመጣልና የመሰብሰብ ስልጣን ለፌደራል መንግስቱ ተሰጥቶ የክልሎች ስልጣን ወደ መካፈል እንዲወርድ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የጋራ ገቢዎች ተብለው የተቀመጡት የክልሎችና የፌደራል መንግስቱ በጋራ የሚያቋቁሟቸወ የልማት ድርጅቶች፣ ህጋዊ ሰውነት ተሰጥቷቸው ከተቋቋሙ ድርጅቶች የሚሰበሰቡ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች፣ የንግድ ትርፍ ግብር፣ ከባለአክሲዮኖች የሚሰበሰብ ታክስ፣ ከከፍተኛ የማዕድን ስራዎች የሚሰበሰቡ ታክሶች እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 62 የጋራ ገቢን አስመልክቶ የሚከፋፈልበትን ቀመር ለፌደሬሽን /ቤት ተሰጥቷል፡፡

ሆኖም አዋጁ እስከ 1995 . ድረስ ተግባራዊ ሳይሆን የቆየ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን የተደነገገው ቀመርም ሳይሻሻል ለረጅም ጊዜ በመቆየቱና በአስተዳደሩ የተለያዩ ክፍተቶች የነበሩበት በመሆኑ በትልልፉ ወቅታዊነት እና ግልፅነት ዙሪያ ከክልሎች በተለያዩ መንገዶች ቅሬታች ሲሰሙ ነበር ተብሏል፡፡

Our Services

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

.