ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸው- የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

Nested Applications

Asset Publisher

Asset Publisher

Asset Publisher

null ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸው- የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የህዝብ ተወካዮች /ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት አፈጻጸም ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም ገምግሟል፡፡

ተቋማቱ በእቅድ የተያዘውን ገቢ በብቃት መሰብሰብ፣ ኮንትሮባንድን እና ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባለፉት ስድስት ወራት የሰሯቸው ስራዎች በአርዓያነት የሚወሰዱ፣ የሚበረታቱና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ስራዎች መሆናቸውን ነው የቋሚ ኮሚቴው አባላት የገለጹት፡፡

የኮሮና ወረርሽኝና ሌሎች በሀገራችን የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ሳይበግሩት የገቢዎች ሚኒስቴር ከእቅድ በላይ ገቢ መሰብሰቡ፣ግብር ከፋዮችንና ስራተኞችን መሸለምና ማበረታታት መጀመሩ፣የሰራተኞችን ብቃት ከፍ ለማድርግ ተከታታይነት ያላቸው ስልጥናዎች ለሰራተኞች መስጠቱ፣በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው ፣ኮንትሮባንድን ለመከላከል የተወሰደው ቆራጥ ዕርምጃ እንዲሁም ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ሚኒስቴር /ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ያደረጓቸው ድጋፎች በጠንካራ ጎን የሚጠቀሱና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ተግባራት መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ / ያየሽ ተስፋሁን ናቸው፡፡

/ ያየሽ አክለውም በጉምሩክ መጋዘን በኮንትሮባንድ ተይዘው የተከማቹ እቃዎች በአግባቡ ቢቀመጡና በጊዜው ቢወገዱ፣ የታክስ መሰረትን ከማስፋት አኳያ ወደ ታክስ መረቡ ያልገቡ ነጋዴዎችን ወደ ታክስ መረቡ የማስገባት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራ፣ ለክልሎች የሚከፋፈለው ገቢ በወቅቱና ህጉን በተከተለ መልኩ ቢፈፀም የሚሉ ጉዳዮች ደግሞ በደካማ ጉን የሚጠቀሱና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸውንም ሰብሳቢዋ አንስተዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸው ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ያቀደውን 290 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ከባለፉት ስድስት ወራት በተሻለ መልኩ ስራዎች በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና ቋሚ ኮሚቴው እንዲስተካከሉ ያላቸውን ጉዳዮች በቀጣይ ተቋሙ በህግ አግባብ እንደሚያስተካክላቸው አስታውቀዋል፡፡

ግብር በፍቃደኝነት የመክፈል ባህል እንዲዳብርና ሁሉም የታክስ ህጎች በአግባቡ እንዲከበሩ በቀጣይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ላይም ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ሚኒስትሩ አክለው ገልፀዋል፡፡ ሀሰተኛ ደረሰኝና ያለ ደረሰኝ የሚፈፀም ግብይት በገቢ አሰባሰቡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ስለሆነ የሚመለከተው አካል ይህንን ህገ ወጥ ደርጊት ለማስቆም ርብርብ እንዲያደርግ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋትና የተለያዩ የአሰራር ስረዓቶችን በመዘርጋት ከባለፈው ጊዜ በተሸለ መልኩ ኮንትሮባንድንና ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የጉምሩክ ኮሚሽን ጠንክሮ እንደሚሰራ የገለፁት ደግሞ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ናቸው፡፡

Our Services

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

.