“ታማኝ ግብር ከፋዮች በሀገራችን ላይ እያኖራችሁት ያለው አሻራ ከፍተኛ እና ትውልድ የማይዘነጋው በጎ ተግባር ነው ” -ወ/ሮ አይናለም ንጉሤ (የገቢዎች ሚኒስትር)

Nested Applications

Asset Publisher

null “ታማኝ ግብር ከፋዮች በሀገራችን ላይ እያኖራችሁት ያለው አሻራ ከፍተኛ እና ትውልድ የማይዘነጋው በጎ ተግባር ነው ” -ወ/ሮ አይናለም ንጉሤ (የገቢዎች ሚኒስትር)

የአራተኛው ዙር የፌደራል ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ስርዓት በትላንትናው እለት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፣ የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል፡፡
በእውቅና እና ሽልማት በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ታማኝ ግብር ከፋዮች ግብራችሁን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል በሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ እያኖራችሁት ያለው አሻራ ከፍተኛ እና ትውልድ ሁሌም የሚዘክረው በጎ ተግባር ስለሆነ አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ በተቃራኒው በግብር መሰወርና ማጭበርበር ተግባር ውስጥ ያላችሁ የንግዱ ማህበረሰብ ክፍል ደግሞ ለህሊናችሁና ለሀገራችሁ ታምናችሁ ወደ ህጋዊ ስርዓቱ ልትመለሱ ይገባል ሲሉ በአፅዕኖት አሳስበዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለውም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በሀገር ፍቅር ስሜት እና በወቅቱ መክፈል ከድህነት ለመውጣት የያዝነውን ቀጠሮ ማሳጠር ስለሆነ ሁሉም ግብር ከፋይ የህይወቱ መርህ ሊያደርገው ይገባልም ብለዋል፡፡
በእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብሩ 400 ታማኝ ግብር ከፋዮች የተሸለሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 40 የሚሆኑት የፕላቲኒየም፣ 120 የወርቅ እና 240 ደግሞ የብር ተሸላሚዎች ሆነዋል። 14 ግብር ከፋዮች ደግሞ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ ተሸላሚ በመሆን ልዩ ተሸላዎች ሲሆኑ አንድ ግብር ሙስናና ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
መሰረታዊ የግብር ከፋይ መረጃ፣ ታክስ ማሳወቅ፣ የግብር ከፋዩ የቅጣት ታሪክ፣ የኦዲት ግኝት ልዩነት፣ የግብር/ታክስ ስሌት ልዩነት እና ሌሎች በድምሩ 12 የሚሆኑ መስፈርቶች ደግሞ ታማኝ ግብር ከፋዮችን ለመመረጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መስፈርቶች ናቸው፡፡

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

"ውጤታማነት በጅማ"

Nested Applications

Asset Publisher

.