ግብር መክፈል የኩራት ምንጭ መሆኑን የሚያምን ማህበረሰብ እንዲፈጠር እንሰራለን! ----------ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ (በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ)

Nested Applications

Asset Publisher

null ግብር መክፈል የኩራት ምንጭ መሆኑን የሚያምን ማህበረሰብ እንዲፈጠር እንሰራለን! ----------ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ (በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ)

በገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ /ቤት 2014 በጀት ዓመት በህግ ተገዢነታቸው ለላቁ ታማኝ ግብር ከፋዮቹ የእውቅና እና ሽልማት ስነ-ስርዓት አካሄደ፡፡

በመድረኩ በህግ ተገዢነታቸው የላቁ 23 ታማኝ ግብር ከፋዮች በፕላቲኒየም፣ በወርቅ እና በሰርተፊኬት ደረጃ አውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የእለቱ የክብር እንግዳ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ  ሚኒስትር ዴኤታ / መሰረት መስቀሌ ግብር መክፈል የኩራት ምንጭ መሆኑን የሚያምን ማህበረሰብ እንዲፈጠር እንሰራለን ያሉ ሲሆን ሁሉን አቀፍ የግብር አሰባሰብ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድረሻ አካል የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም የድሬደዋ ቅርንጫፍ /ቤት ከእቅድ በላይ ገቢ እንዲሰበሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የቅርንጫፉ ስራአስኪያጆችና ሰራተኞች እንዲሁም ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ተሸላሚ ግብር ከፋዮች ግብርን በታማኝነት የመክፈል ተግባራቸውንም አጠናክርው እዲቀጥሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የድሬደዋ ቅርንጫፉ /ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አትሃም መሐመድ በበኩላቸው ለሀገር ኢኮኖሚ አቅም መጎልበት እና ለጠንካራ ኢኮኖሚ መሰረት ለመሆን ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና ፍታሃዊ የሆነ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን ገቢን ለመሰብሰብ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተሻለ የህግ ተገዢነትን ላሳዩ የግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት መስጠት ተገቢ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሌላው በዚሁ መድረክ ግብር ከፋዮችን በታክስ ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥን በተመለከተ በሞጁላር ሥልጠና ላይ ሰነድ ያቀረቡት የታክስ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍርዱ መሰረት ሀገራዊ ወጪን በሀገራዊ ገቢ ለመሸፈን የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት አጠቃላይ ማህበረሰቡን፣ መጭውን ትውልድ እና ግብር ከፋዮችን በሞጁል በተደራጀ መልኩ የታክስ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን 90 ግብር ከፋዮች 46 ከድሬደዋ እና 44 ከሀረር ከተማ የተውጣጡ ግብር ከፋዮች 90 ሰዓት ስልጠና ወስደው ለማስመረቅ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የዝግጅቱ ተሳታፊዎች እና ተሸላሚዎች በበኩላቸው በእውቅናው እና በመሸለማቸው እጅግ ደስተኞች እና ክብር የሚሰማቸው መሆናቸውን ተናግረው በቀጣይም ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል ለሌሎች ግብር ከፋዮች ምሳሌ ሆነው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር የሁሉም ክልሎች የገቢ ዘርፍ አመራሮች በታክስ ምንነት፣ ህጎችና አዋጆች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና Wed, 4 Jan 2023
የገቢዎች ሚኒስቴር የሁሉም ክልሎች የገቢ ዘርፍ አመራሮች በታክስ ምንነት፣ ህጎችና አዋጆች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
  • ግብር መክፈል የኩራት ምንጭ መሆኑን የሚያምን ማህበረሰብ እንዲፈጠር እንሰራለን! ----------ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ (በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ) Wed, 4 Jan 2023
ግብር መክፈል የኩራት ምንጭ መሆኑን የሚያምን ማህበረሰብ እንዲፈጠር እንሰራለን! ----------ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ (በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ)
  • የሀገራችንን ወጪ በታክስ ገቢ ለመሸፈን የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና ከፍተኛ ነው -- ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ (የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ) Wed, 4 Jan 2023
የሀገራችንን ወጪ በታክስ ገቢ ለመሸፈን የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና ከፍተኛ ነው -- ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ (የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ)

የኤሌክትሮኒክስ ታክስ የማስታወቂያ ዘዴ /E-tax/ ማሻሻያ የተደረገባቸው የታክስ ማስታወቂያ ቅፆች

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

.