በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ512 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል

Nested Applications

Asset Publisher

null በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ512 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል

ሐምሌ 21/ 2016 . (ገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን 2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ  በአርባምንጭ ከተማ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

በመድረኩ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 529.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 512 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር / ዓይናለም ንጉሴ ገልጸዋል፡፡

ከአምናው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ገቢው 70 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም ዘመናዊ እና ተደራሽ የታክስና የጉምሩክ አስተዳደር ስርዓትን በመገንባት አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረፅ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ በማድረግ የዕቅዱን 96 በመቶ በላይ እንዲሳካ አስችሏል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ህገወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ በሀገራዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ ገልፀው፤ በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ህጋዊነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ትብብር እንዲያደርጉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher

ዜና

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.