ባለፉት 6 ወራት ከእቅድ በላይ ገቢ ተሰበሰበ

Nested Applications

Asset Publisher

null ባለፉት 6 ወራት ከእቅድ በላይ ገቢ ተሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት ለመሰብሰብ ካቀደው 146.9 ቢሊየን ብር 149.2 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 102 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ጥር 24  ቀን 2013 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አፈፃፀሙ ከባለፋው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 21.6 ቢሊየን ብር ወይም 17 በመቶ እድገት ማሳየቱንና የተሰበሰበው ገቢ ከገቢ አርዕስቶች አንፃር ሲታይ ከሀገር ውሥጥ ገቢ 93.3 ቢሊየን ፣ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 55.7 ቢሊየን እና ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የተጣራ ትርፍ 130 ሚሊየን ብር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዕቅዱ ላይ በዝግጂት ምዕራፍ አመራሮችና ሰራተኞች ተግባብተውና የጋራ አቋም ይዘው መስራት መቻላቸው፣ጠንካራ የሆነ የድጋፍና ክትትል ስራዎች መሰራታቸው፣በቴክኖሎጂ የተደገፍ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ከቅ//ቤቶች ጋር በየሳምንቱ ጠንካራ የግምገማና የልምድ ልውውጥ እንዲሁም ለስራ እንቅፋት የሆኑ ችግሮች ከስር ከስር እየተፈቱ መሄዳቸው እና በየደረጃው ያሉ አመራርና ሰራተኞች ስራቸውን በአግባቡ መከወን መቻላቸው የተያዘው እቅድ ሊሳካ እንዳስቻለ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አክለው ማህበራዊ ሀላፊነትን ከመወጣት አንፃርም ባለፉት ስድስት ወራት በሚኒስቴር /ቤቱና በተጠሪ ተቋማት የሚሰሩ አመራርና ሰራተኞች ከደሞዛቸው 800 ብር በላይ በማዋጣት 209 ተማሪዎችን በቋሚነት እየረዱ እንደሚገኙና ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክትም 58.3 ሚሊየን ብር በላይ ከደሞዛቸው እየተቆረጠ ገቢ እየተደረገ እንደሆነ እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 442.7 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ እንደተደረገ አንስተዋል፡፡ለእቅዱ ስኬት በየደረጃው ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

"ውጤታማነት በጅማ"

Nested Applications

Asset Publisher

.