Asset Publisher

null የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ለወሎ ዩኒቨርስቲ የተለያዩ ድጋፎችን አደረጉ

የገቢዎች ሚኒስቴር እና  የጉምሩክ ኮሚሽን  ለወሎ ዩኒቨርስቲ 50 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን እና አምስት የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደርገዋል ::

ድጋፉን የገቢዎች ሚኒሰቴር  ሚኒስትር / ዓይናለም ንጉሴ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ለዶ/ መንገሻ አየለ በደሴ ከተማ አስረክበዋል ::

በድጋፍ ርክክቡ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር / ዓይናለም ንጉሴ ዩኒቨርስቲው ለገጠሙት ችግሮች እጅ ሳይሰጥ ችግርን ወደ እድል በመቀየር በአፋጣኝ ወደ መማር ማስተማር ስራው በመግባቱ ከፍተኛ ምስጋናንን አቅርበዋል።

''የጉምሩክ ኮሚሽን ከዮኒቨርስቲው ጋር ያለው ግንኙነት በመስጠት እና በመቀበል ላይ ብቻ ያተኮረ አይደለም " ያሉት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በቀጣይ አንኳር በሆኑ ስትራቴጃዊ ጉዳዮች ላይ ከዩኒቨርስቲው ጋር ለመስራት የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

የወሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት / መንገሻ አየለ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሰቲው በጦርነቱ ምክንያት 12 ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት እንደደረሰበት ገልጸዋል።

ዮኒቨርስቲው በአጭር ጊዜ ተደራጅቶ ወደ ሥራ እንዲገባ የሁለቱ ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ፕሬዝደንቱ ጠቅሰው፣ ስለተደረገው ድጋፍም አመስግነዋል።

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)