Asset Publisher

null ከ107.8 ቢለየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት ለመሰብሰብ ካደቀው 104.5 ቢሊየን ብር በላይ 107.8 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ህዳር 11/2013 ዓ.ም  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 17.3 ቢሊየን ብር እድገት ማሳየቱን ጠቅሰው የህግ ተገዢነት ደረጃ መሻሻል፣ የተቋሙ ሰራተኛና አመራሮች ቁርጠኝነት መጨመር እና የገቢው መሰረትን ለማስፋት የተደረጉ ጥረቶች ገቢው እንዲጨምር ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ላቀ የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችም በአራት ወራት መጠናከራቸውን ለገቢ አሰባሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው ብለዋል፡፡

ህግን ለማስከበር ከተከናወኑ ተግብራት መካከል የኮንትሮባንድ ክትትል አንዱ ሲሆን በወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ 1.08 ቢሊየን ብር የተገኘ ሲሆን የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አካላት፣ የጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በፌደሬሽን ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት የክልል እና የፌደራል መንግስት ገቢ ክፍፍልን ወደ ተግባር በመቀየር ባለፉት አራት ወራት 3.9 ቢሊየን ብር በላይ ለክልሎች መተላለፉን የገለጹት ሚኒስትሩ ተቋሙ ባለፉት ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱንም እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአራት ወራት ውስጥ በዝግጅት ምዕራፍ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ግብር ከፋዮችን በከፈሉት የገንዘብ መጠን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ መስፈርቶችን ባካተተ መልኩ ምደባ በመስጠት የታክስ ህግ ተገዢነትን ለማሳደግ እንዲሁም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ደግሞ ተጨማሪ ቅርንጫፍ /ቤቶች መከፈታቸውን እንዲሁም የህግ ተገዢነትን ለማጎልበት 2012 . በታማኝነት ግብራቸውን ለከፈሉ ግብር ከፋዮች እውቅና መሰጠቱን አንስተዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በቀጣይ ጉድለቶችን በማረም፣ የአሰራር ችግሮችን በመቅረፍ ግልጽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ላቀ በታማኝነት ግብራቸውን ለሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ምስጋናቸውን አቅርበው በተለይ ሀገር በብዙ ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ሰዓት ግብር ከፋዩ ከሚያገኘው ላይ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ሊያሳይ ይገባል ብለዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)