Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Most Viewed Assets

null 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል

እስካሁን በተሰራ ስራ 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት መቻሉን የአንድ መስኮት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ተስፋዬ ለተጠቃሚዎች ስልጠና በተሠጠበቅ ወቅት ገልፀዋል፡፡ ስልጠናን ጨምሮ በቪዲዮ የታገዘ መረጃዎችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎችን ከአገልግሎቱ ጋር የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት ያደጉ ሀገራትና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የንግድ ተወዳዳሪነትን ከፍ ለማድረግ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡

በኢትዮጵያም 16 የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎትን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

የአገሪቱን የገቢና ወጪ አገልግሎት ግልፅነት የጎደለው፣ ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ እንዲሁም አገልግሎቱን ለማገኘት በርካታ ጊዜ ይጠፋ እንደነበር ያነሱት አቶ ሮቤል ተስፋየ የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት እነዚህንና መሰል ችግሮች በመፍታት በኩል የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣዮቹ ስድስት ወራት እስከ 3 ሰልጣኞች ከአገልግሎቱ ጋር የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ ነው የገለፁት፡፡

የአንድ መስኮት አገልግሎትን ቀደም ሲል እየተጠቀሙበት እንደሚገኙና ጊዜና ገንዘባቸውን ከአላስፈላጊ ወጭ እንዳዳነላቸው አስተያየታቸውን የሰጡን ሰልጣኞች የገለፁ ሲሆን ስልጠናው በአጠቃቀም ወቅት ይገጥማቸው የነበረውን ችግር እንደሚቀርፍላቸው አንስተዋል፡፡