በመቶ ቀናት እቅድ 108.9 ቢሊዮን ብር እንዲሰበሰብ አቅጣጫ ተሰጠ

ጥቅምት 16 / 2014 . (ገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2014 . ድረስ በመቶ ቀናት የሚከናወኑ ስራዎችን እቅድ በተመለከተ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

በነዚህ መቶ ቀናትም 108.9 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እቅዱን ለመሳካት ደግሞ አምስቱን ስትራቴጂክ የውጤት መስኮች ማለትም በአሰራር ስርዓት፣ በህግ ተገዥነት አመራር ልዕቀት፣ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ልዕቀት፣ ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አቅም ልማት እና ዘላቂ የገቢ እድገት ላይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ዝርዝር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመቶ ቀናት በአሰራር ስርዓት ላይ በሀገር ውስጥ ታክስ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች የሚሰጡ ምላሾችን ወደ 85 በመቶ ለማሳደግ፣ በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች የሚሰጡ ምላሾችን ወደ 87 በመቶ ለማሳደግ፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ አምስቱ ቅርንጫፍ /ቤቶች በኢ-ታክስ የሚያሳውቁ ግብር ከፋዮች ድርሻን ወደ 100 ፐርሰንት ለማድረስ የሀገር ውስጥ ታክስ ተገልጋይ ዕርካታን ወደ 78 በመቶ ማሻሻል የሚሉና ሌሎች እቅዶች ተይዘዋል፡፡

1,839 በስጋት የተመረጡ ማህደራትን የታክስ ኦዲት ለማከናወን፣ 114 በታክስ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ማህደራትን ኢንቨስቲጌሽን ኦዲት ለማድረግ፣ የጉምሩክ ኢንተለጀንስ ውጤታማነትን ወደ 70 በመቶ ለማሻሻል፣ 1.1 ቢሊዮን ብር የሚገመት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ መከላከልና መቆጣጠር የሚሉ እና ሌሎችም እቅዶች ተይዘዋል፡፡

ስትራቴጂያዊ አጋርነት ልህቀት አኳያ በሀገር ውስጥና ከዉጪ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ሶስት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም ከአጋር አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚበቅም በዕቅዱ ላይ ተቀምጧል፡፡

ውይይቱን የመሩት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ለታቀዱት ስራዎች ተግባራዊነት የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በትልቅ ተነሳሽነት እንዲንቀሳቀሱ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ከፍተኛ አመራሩም የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ በመስራት እና ሁሉም ኃላፊነቱን በመወጣት የገቢ እቅዱን ለማሳካት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል Fri, 29 Oct 2021
10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል