ሚኒስቴሩ ከ 200 በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን መያዙን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፌደራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት ባደረገዉ ክትትልና ቁጥጥር 200 በላይ የሽያጭ መመዝገቢያዎችን መያዝ መቻሉን በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበርና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዡ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡

የሽያጭ መመዝገቢያዎቹ የተያዙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሆኑን የገለፁት ሃላፊዉ በአንድ ህንጻ ዉስጥ ተከማችተዉ ግዢና ሽያጭ በሌለበት ህገ ወጥ ቦታ መገኘታቸዉንም አክለዉ ገልፀዋል፡፡

በዚህ ድርጊት የተሰማሩት እነዚህ አካላት ሃሰተኛ ደረሰኞችን ግብይት እንደተካሄደ አስመስለዉ በመቁረጥ በታክስ አስተዳደር ስርአቱን የሚጎዳና የንግድ ማጭበርበር መፈፀማቸዉን መግለጫዉ ተነስቷል፡፡

በምርመራዉ ግኝቱ 90 በመቶ የሚሆኑት በአስመጭነት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ አለም አቀፍ ድርጅቶችም የሚገኙበት መሆኑን ተመላክቷል፡፡

ስስካሁን በተደረገዉ የምርመራ ግኝት ዉስጥ 40 ባለቤት የሌላቸዉ የሽያጭ መመዝገቢያዎችን መለየት መቻሉንም ጭምር በምርመራዉ ታዉቋል፡፡

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የታክስ እና ጉምሩክ ወንጀል ምርመራ ዳሬክተር አቶ ብርሃኑ አባተ በበኩላቸዉ ድርጊቱ በርካታ ተዋናዮች ያሉበትና በቀጣይ ሰፊ ምርመራ የሚያስፈልገዉ መሆኑን ገልፀዉ ተቆጣጣሪ አካላት ሃላፊነታቸዉን በሚገባ ከመወጣት አኳያ መታየት ያለበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ መሰል ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ የሚያደርገዉን ጥቆማ እና ትብብር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ሃላፊዉ አክለዉ አሳስበዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)