ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው

ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው

የገቢዎች ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች ከደሞዛቸው በተዋጣ 2 ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ብር በላይ በማወጣት ዝቅተኛ ደሞወዝ ላላቸው (ደረጃ አምስት በታች ላሉ) ሁሉም ሰራተኞች ለእያንዳድዳቸው የ50 ኪሎ ግራም ጤፍ ድጋፍ አደረገ፡፡
ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው እንዲሉ በአለማቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ጫና እና ማነኛውንም ችግር ለመቋቋም የመተጋገዝ፣ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ኢትዮጵያዊ ባህላችንን ማጎልበት አለብን ያሉት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ናቸው፡፡ አቶ ላቀ አያይዘውም ከወር ደሞወዛቸው ቀንሰው ይህን ድጋፍ ያደረጉ ሰራተኞችን፣ ያስተባበሩ ኮሚቴዎችን እና አመራሮችን አመስግነው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ...እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ ከተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች በወር 0.5% ከደሞዛቸው ተዋጦ በHIVኤድስ የተጠቁ ሰራተኞችን ለመርዳት ከሚውል ገንዘብና በተጨማሪ 57 ሺህ ብር በመዋጣት በድምሩ 2 ሚሊየን 425 ሺህ ብር ድጋፍ የተደረገ መሆኑን የገለጽት የተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ምህረት ምናስብ በጤፍ አቅርቦቱ እገዛ ያደረውን የሞጣ ዩኒየንን አመስግነዋል፡፡
ሠራተኞቹ በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ ተቋሙ ወረርሽኙ ያስከተላው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግር ለመቋቋም ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Mon, 1 Mar 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል Thu, 3 Dec 2020
10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል