የ 100 የአቅመ ደካማ እና የአረጋዊያንን የቤት እድሳትና ግንባታ ተጀመረ

የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአዲስ አበባ የሚገኙ የአንድ መቶ የአቅመ ደካማና የአረጋዊያንን ቤት ለመገንባት 10 ሚሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር አስረክበዋል፡፡

የቤቶቹ አድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በየካ ክፍለ ከተማ ተጀምሯል፡፡

ለቤቶቹ እድሳት በጋራ ያዋጡትን 10 ሚሊዮን ብር የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ለአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ባስረከቡበት ወቅት የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን ልጆችን ማስተማር በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በማገዝና በመደገፍ፣ በኤች አይቪ ኤድስ የተያዙ ወገኖችን ማገዝና መርዳት እንዲሁም ቋሚ የሆነ የችግኝ መትከያ ቦታ በመውሰድ በመትከልና በመንከባከብ ባላፉት ሁለት አመታት ከመደበኛው ስራቸው ጎን ለጎን ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ሲያከናውኗቸው የነበሩ ተግባራት መሆናቸውን በመጥቀስ በዘንድሮው ዓመትም 100 የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ ለነዋሪዎቹ ለማስረከብ ስራው ዛሬ መጀመሩን አብስረዋል።

በስነስርዓቱ ላይ የተገኙትና ለግንባታ ወጭ የሚውለውን 10 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ቼኩን የተቀበሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከለውጡ ወዲህ እንደባህል እየሆነ መምጣቱን በመጥቀስ ከተማ አስተዳደሩ ከያዛቸው 14 ዓይነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መካከል በዚህ ዓመት 2 የአቅመ ደካማና የአረጋዊያንን ቤት ለማደስና ለመገንባት ዕቅድ መያዙንና ከዚህም ውስጥ የገቢዎች ሚኒስቴር 100 ቤቶችን ለመገንባትና ለማደስ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በመዲናዋ የሚኖሩ የዕድሉ ተጠቃሚ አረጋዊያንና አቀመ ደካሞችም የገቢዎች ሚኒስቴር ችግራችንን አይቶ እና ተረድቶ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ቤታችንን ስለገነባልንና ስላደሰልን እናመሰግናለን ፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Sat, 18 Sep 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል Thu, 22 Jul 2021
10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል