የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን - mor

Nested Applications

Asset Publisher

Asset Publisher

News

  • The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission. Wed, 13 Dec 2023
The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission.
  • Excise tax training  Wed, 13 Dec 2023
Excise tax training 
  • The World bank's willingness to support the revenue sector Mon, 11 Dec 2023
The World bank's willingness to support the revenue sector

services

Our Services

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

null የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን

 

ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባቀረጥና ታክስ የሚታሰበው የተሸከርካሪዉን ሲሲ መሰረት በማድረግ  CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡ ተሽከርካሪው ያገለገለ ከሆነ ከተመረተበት አንድ ዓመት ጊዜ ጀምሮ ከFOB ዋጋዉ ላይ በየዓመቱ 10% በመቀነስ በጠቅላላዉ እስከ 3 አመት ወይም 30% ድረስ የእርጅና ቅናሽ ካለዉ በማስላት የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ በማባዛት ቀረጥና ታክሱን ማወቅ ይቻላል፡፡

የተሽከርካሪው የፈረስ ጉልበት ማለትም ሲሲው 1300 ከሆነ 125%ሲሆን 1301ሲሲ እስከ 2500 ሲሲ ደግሞ ከ176.24% እስከ 244.55% ባሉትየጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ ይሰላል፡፡ለሰው ማጓጓዣ የሚያገለግሉ ሌሎች ተሸከርካሪዎች ሲሆን ደግሞ በሌላ ስፍራ ያልተጠቀሰ ከሆነ የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ 125.00075% ሲሆን ሹፌሩን ጨምሮ አስር ወይም ከዛ በላይ ሰዎችን ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሸከርካሪዎች ከ15 ተጓዦች ያነሰ መቀመጫ ያላቸው ተሸከርካሪዎች 58.25% እንዲሁም 15 እና ከዚያ በላይ ሰው የሚይዝ መቀመጫ ያላቸው የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔው 29.50% ነው፡፡ 

የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ የተሸከርካሪ ቀረጥና ታክስ ለመወሰን አምስት የሰሌት ደረጃዎችን(ማለትም የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ) እንከተላለን፡፡ የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ በምሳሌ እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ሲገባ:-

በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35% =24,500 ይሆናል፡፡

ቀጥሎ ኤክሳይስ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) 30%=28,350 ይሆናል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350) 15% = 18,427.5 ብር ይሆናል፡፡

በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350 +18,427.5)10%= 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡

በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70,000 X 3%= 2,100 ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት

24,500 + 28,350 + 18,427.5 + 14,127.75 + 2,100= 87,505.25 ብር ይሆናል፡፡

important links