የገቢዎች ሚኒስቴር የአገር በቀል ኢኮኖሚ ዕቅድ ለማሳካት ተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እየሰራ ይገኛል።

 

የገቢዎች ሚኒስቴር የአገር በቀል ኢኮኖሚ ዕቅድ ለማሳካት ተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እየሰራ ይገኛል።

የገቢዎች ሚኒስቴር የአገር በቀል ኢኮኖሚ ዕቅድ ለማሳካት ተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እየሰራ ይገኛል።
************************************************************************************************
መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ እቅዱን ለማሳካት ከአጋር አገራት የ10 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱን ገልፀው እቅዱን ለማሳካት ተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር ስለሚያስፈልግ የገቢዎች ሚኒስቴር ተጨማሪ የ20 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እየሰራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ለአገር በቀል ኢኮኖሚ ኘሮግራም ለመሰብሰብ የታሰበው ይህ 20 ቢሊዮን ብር እስካሁን መሰብሰብ ያልተጀመረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ በኃላ መሰብሰብ እንደሚጀመር ተገልጿል። ስለሆነም የግብር /የታክስ ከፋዮቹም ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በታመኝነትና በወቅቱ የሚጠበቅባቸውን ግብር በመክፈል ግዴታቸውን እንዲወጡ ገልፀው ሁላችንም እንደተለመደው ሁሉ ለአገራዊ ጥሪው የበኩላችንን ሚና መወጣት እንደሚያስፈልግም ተናግሯል።
ክብርት ሚኒስቴሯ አክለውም ሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ አምና በዚህ ወቅት የሰበሰበው 98 ቢሊዮን ብር አካባቢ መሆኑን ገልፀው ዘንድሮ ደግሞ በተደረገው ርብርብ በ6 ወራት ብቻ 127.5 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ተችለዋልብለዋል። ቀሪውን እቅዳችንንና ለአገር በቀል ኢኮኖሚ ኘግሮራም ለማሰካት ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ የተዘጋጀውን እቅድ በቁርጠኝነት በመስራት ማከናወን እንችላለን ብለዋል።
ስለሆነም የሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች: ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ ለእቅዱ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ክብርት ሚኒስትሯ ጥሪያቸውን አስተላልፏል።

.

Latest News

  • The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission. Wed, 13 Dec 2023
The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission.
  • Excise tax training  Wed, 13 Dec 2023
Excise tax training