የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ባንኮች ኢ-ፔይመንትን በተቀላጠፈ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ለታክስ አሰባሰቡ ቀልጣፋ እና ዘመናዊነት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ የታክስ አሰባሰቡን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ የባንኮች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ባንኮች የደንበኞቻቸውን ግብር ክፍያ በወቅቱ በማስተላለፍ ካላስፈላጊ ወለድ እና ቅጣት ሊታደጓቸው እንደሚገባ እንዲሁም የግብር ሰብሳቢው ተቋም ለግብር አሰባሰቡ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች በወቅቱ እና በግልጸኝነት በመስጠት ሊተባበሩ ይገባል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለውም የገቢዎች ሚኒስቴር አስፈላጊ የሆኑ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የክፍያ ስርዓቶች ላይ ማሻሻያዎችን ማድረጉን የጠቆሙ ሲሆን ባንኮች እንደ ግብር ከፋይ ብቻ ሳይሆን እንደ አገልገሎት ሰጪ ተቋም ለግብር አሰባሰቡ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተያያዘ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር በበኩላቸው ከሀገራዊ ኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር ተያይዞ የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ስለዚህም የፋይናንስ ተቋማት ሀገራዊ ዲጂታይላዜሽን አውን ከማድርግ እና ግብርን በተቀላጠፈ ሁኔታ መሰብሰብ እንዲቻል ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የባንኮች ተወካዮች ለታክስ አሰባሰቡ ቀልጣፋነት አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የገለጹ ሲሆን በስራው ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በንግግር እና በትብብር ለመፍታት እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡
በብዛት የተነበቡ ዜናዎች
-
Fri, 29 Oct 2021"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
-
Wed, 4 Jan 2023"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)