faq

በገቢዎች ሚኒስቴር በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸዉ

 

Q1. የሽያጭመመዝገቢያ መሳሪያ /Cash Register Machine/ ተጠቃሚዎች ማሽኑ ብልሽት ሲያጋጥመው መብራት በሚጠፋበት ወቅት እንዲሁም የአድራሻ ለውጥ በሚያደርጉበት ጊዜ ያለው አጠቃላይ መረጃ ቢብራራ?

መልስ. የሽያጭመመዝገቢያ መሳሪያው ብልሽት በሚያጋጥምበት ጊዜ ለአገልግሎት ማዕከሉ እና ለባለስልጣን መ/ቤቱ በ2 ሰዓት ውስጥ ማሳወቅ መብራት በሚጠፋበት ጊዜ ለባላስልጣን መ/ቤቱ ወድያውኑ በስልክ ወይም በአካል ማሳወቅ፣ አድራሻ ለውጥ በሚፈልጉ ጊዜ አድራሻ ለውጥ ያደረጉበትን ንግድ ፈቃድ እና መመልከቻ በማያያዝ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ማቅረብ ያለባቸው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Q2. የወጭ መጋራት ክፍያ /cost sharing/ ክሊራንስ በክፍሎች ይሰጣል?

መልስ. ተማሪዎች ለእንግልት እና ለተጨማሪ ወጪ ሳይዳረጉ አገልግሎት ከሰጡበት ተቋም የሚፈለግባቸውን ክፍያ /አገልግሎት/ ስለማጠናቀቃቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ሰጽፈው ሲቀርቡ በአካባቢያቸው ከሚገኘው ገቢ ሰብሳቢ ቅ/ጽ/ቤት ክሊራንስ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገለፃለን፡፡

Q3. የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ /cost sharing/ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኃላ በምን ያህል ጊዜ ገንዘብ መክፈል እንደሚገባ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር እንዲሁም አጠቃላይ ያለው ሁኔታ በዝርዝር ቢገለጽ?

መልስ. የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ /cost sharing/ በተመለከተ ከአንድ ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኃላ ክፍያው መጀመር ያለበት ሲሆን፤ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር በጤናና በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡበትንና አገልግሎት የሰጡበትን ማስረጃ በማቅረብ ወደሚገኘው ገቢ ሰብሳቢ ቅ/ፅ/ቤት በመሄድ መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Q4. ወደ ውጭ ምርቶቻቸውን የሚልኩ ባለሃብቶች በሚልኩበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 0% ሆኖ ሳለ ቫት/VAT/ ተመዝጋቢ የመሆናቸው ምክንያት በግልጽ ቢብራራ?

መልስ. ወደ ውጪ ምርቶቻቸውን የሚልኩ ባለሃብቶች የዜሮ ተመን ቫት ተመዝጋቢ የመሆናቸው ምክንያት ለግብዓት የተከፈለውን ታክስ ተማላሽ ለማድረግና የውጭ ንግዱን ከማበረታታት አንፃር ነው፡፡

Q5. ቅጣት ብቻ የተጣለበት ግብር ከፋይ ቅጣት እንዲነሳለት በሚጠይቅበት ጊዜ ስንት መቶኛ ይነሳለታል?

መልስ. አስተዳዳራዊ መቀመጫዎች እንደማይነሱ ከተገለፁት ሁኔታዎች በስተቀር በግብርና ታክስ ላይ የተጣሉ አስተዳደራዊ መቀመጫዎች እንደሁኔታው በሙሉ ወይም በከፊል ሊነሱ ይችላሉ፡፡

Q6. በኢትዮጵያ ነዋሪ ሆኖ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ የሌለው ሰው በሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ላይ ምን ያህል % ነው ግብር የሚከፍለው?

መልስ. ቅድመ ግብር ክፍያ ቀንሰው እንዲስቀሩ ሀላፊነት የተጣለባቸው አካላት አገልግሎቱን ያቀረቡ ሰዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከሌላቸው 30% (ሰላሳ ፐርሰንት) ቀንሰው ገቢ እንዲያደርጉ በህጉ ተደንግጓል፡፡