Asset Publisher

ዜና

  • የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል Tue, 29 Oct 2024
የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል
  • የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ Tue, 29 Oct 2024
የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

Most Viewed Assets

null "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እና የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ የኮምቦልቻ ጉምሩክ እና ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ የስራ መመሪያ የሰጡት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ የኮምቦልቻ ገቢዎች እና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በደረሰባቸው ውድመት ከመቆዘም ወጥተው በፍጥነት ወደ ስራ መግባታቸው አመራሩ እና ሰራተኛው ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት እና ትጋት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ያቀድነውን ብቻ ሳይሆን ካቀድነው በላይ ለመፈጸም እንሰራለንም ብለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው፣ ሁለቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚካሄድበት አካባቢ የሚገኙ በመሆናቸው ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት መሰብሰብ የሚያስችል ፈጣን እና የደንበኞችን ፍላጎት የሚያረካ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ያለን አማራጭ ልማት እና ብልጽግና ብቻ ነው ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ፤ ይህን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል::

በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ያስታወሱት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራአስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ፣ አመራሩ እና ሰራተኛው በደረሰው ውድመት ሳይደናገጥ በርትቶ በመስራቱ አሁንላይ የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የስራ ከባቢን መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡