የኤክሳይዝ ታክስ አስተዳደራዊ ቅጣቶች
ኤክሳይዝ ታክስን በተመለከተ ለሚፈጸም ጥፋት የሚወሰዱ አስተዳደራዊ ቅጣቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ፍቃድ ሳይኖረው የኤክሣይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ዕቃዎች የሚያመርት ሊከፈል የሚገባውን የኤክሣይዝ ታክስ እጥፍ፣
2. የኤክሣይዝ ቴምብር ሊለጠፍባቸው የሚገቡ ዕቃዎችን ቴምብር ሳይለጠፍባቸው የተገበያየ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ እጥፍ፣
3. በፍቃዱ ከተመለከተው ቦታ ውጪ ሲያመርት የተገኘ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ እጥፍ፣
4. ከኤክሣይዝ ታክስ ቁጥጥር ውጪ ዕቃ ወጪ አድርጎ የተገኘ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ እጥፍ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡