የገቢዎች ሚኒስቴር በደም ልገሳ ላሳየው ንቁ ተሳትፎ እውቅና ተሰጠው

ጥር 28/2013 .

ብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች የደም እጥረት እንዳያጋጥም ደም በመለገስ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ላሳዩ የመንግስት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙሃን ጥር 27/2013 . በስካይ ላይት ሆቴል ባዘጋጀው የምስጋና መርሃ ግብር እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ከመደበኛ ገቢ የመሰብሰብ ስራው ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነትን እየተወጣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በህግ ማስከበር ሂደቱ የደም እጥረት እንዳያጋጥም በስሩ ያሉ ተቋማትን በማስተባበር ላበረከተው ግንባር ቀደም ተሳትፎ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ በዕወቅና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተበረከተው የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተረክበዋል፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል በንቲ በበኩላቸው ደም በመለገስ ወገኞቻችንን ህይወት መታደግ ታላቅነትና ወገናዊነትን ማሳያ በመሆኑ በዚህ በጎ ተግባር የተሳተፉ አካላትን በማመስገን ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በስሩ ያሉትን ጉምሩክ ኮሚሽንንና ብሄራዊ ሎተሪ ሰራተኞችን በማስተባበር ደም ልገሳ ጥሪውን በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍ ከፍተኛ ወገናዊነቱን አሳይቷል፡፡

ደም መለገስ ከሁሉ ስጦታዎች በላይ ነው ያሉት የጤና ሚኒስትሯ / ሊያ ታደሰ በዚህ በጎ ተግባር የተሳተፉ አካላትን አመስግነው በቀጣይም ተቋማት ደም የመለገስ ተግባር ባህል አድርገው ሊያስቀጥሉት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)