Asset Publisher

null የሀገራችንን ወጪ በታክስ ገቢ ለመሸፈን የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና ከፍተኛ ነው -- ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ (የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ)

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት የተሻለ የህግ ተገዥነት ላሳዩ እና ግብራቸውን በወቅቱና በታማኝነት ለከፈሉ 83 ታማኝ ግብር ከፋዮች  በቅ//ቤት ደረጃ እውቅና ሰጥቷል፡፡

በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ / መሠረት መስቀሌ የሀገራችንን ወጪ በታክስ ገቢ ለመሽፈን ለምናደርገው ጉዞ የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ሁሉም ግብር ከፋይ ለራሱ እና ለሀገሩ ታማኝ ሆኖ የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ በመክፈል ሀገራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም ግብር የሚሰውሩና የሚያጭበረብሩ አካላትም ከእኩይ ድርጊታቸው ተቆጥበው ለሀገር አለኝታ በመሆን ተሸላሚ ሊሆኑ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቅ//ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ታምሩ በበኩላቸው ሁሉም ግብር ከፋይ የግብር ግዴታውን በወቅቱና በታማኝነት በመወጣት የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ልናፋጥን ይገባል ብለዋል፡፡ //ቤቱም ባለፉት አምስት ወራት በሰራው ጠንካራ የገቢ አሰባሰብ ስራ 4 ነጥብ 364 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 123 በመቶ ማሳካት መቻሉን እና ለተገኘው ውጤትም ግብራቸውን በታማኝነት እና በወቅቱ በመክፈል አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግብር ከፋዮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ታማኝ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው የተሰጣቸው እውቅና ይበልጥ ለግብር ህጉ ታማኝ እና ተገዥ በመሆን ግብራቸውን በታማኝነት እንዲከፍሉ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልፀው ሌሎች ግብር ከፋዮችም የእነሱን አርዓያነት ተከትለው ግብራቸውን በአግባቡ በመክፈል ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተልልፈዋል፡፡

የተሟላ መሰረታዊ የግብር ከፋይ መረጃ፣ ታክስ ማሳወቅ፣ የግብር/ታክስ ስሌት ልዩነት፣ የኦዲት ግኝት ልዩነት እና ሌሎች 12 ሚሆኑ መመዘኛዎች ደግሞ ታማኝ ግብር ከፋዮችን ለመሸለም ጥቅም ላይ የዋሉ መስፈርቶች ናቸው፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)