የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገለጸ
ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ዘርፍ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት እያካሔደ ይገኛል።
በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ እንዳሉት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ከባለፉት ዓመታት አንጻር ከፍተኛ ቢሆንም በገቢ አሰባሰብ ጥሩ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ለእቅዱ መሳካትም ከሁሉም ሰራተኛ ውጤታማ እርብርብ በተጨማሪ አስቻይ ሁኔታዎችን በሚገባ መለየት መቻሉ፣ ተቋማዊ ሪፎርም ተጠናክሮ መሰራቱ፣ የሕግ ማስከበር ስራው ውጤታማ መሆኑ፣ የታክስ እና ጉምሩክ ንቅናቄ በትኩረት መሰራቱ ውጤታማ የታክስ አሰባስብ እንዲኖር ጉልህ ሚና ነበረው ብለዋል።
አያይዘውም የ2017 በጀት ዓመት እቅድን ማሳካት የሚቻለው በዋነኝነት የሁሉም የተቋሙ ሰራተኛ ርብርብ ሲኖር መሆኑን በመገንዘብ አመራሩ እና ፈጻሚው በእቅዱ ላይ በንቃት ተወያይቶ የጋራ እቋም በመያዝ ውጤታማ እንደሚያደርግ ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ በሚኒስቴሩ የታክስ ስርዓት ዘርፍ አማካሪ አቶ ሂካ ባርባ የዘርፉን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ለውይይት አቅርበዋል።
በብዛት የተነበቡ ዜናዎች
-
Fri, 29 Oct 2021"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
-
Wed, 4 Jan 2023"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)