የጉምሩክ ኮሚሽን ለሽያጭ ያቀረባቸው ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ መሆኑ ኮሚሽኑ ገለፀ፡፡ ሕዳር 14፣ 2016 ዓ.ም. (የገቢዎች ሚኒስቴር)

Nested Applications

Asset Publisher

የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል

የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል Tue, 29 Oct 2024

የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ Tue, 29 Oct 2024

Asset Publisher

null የጉምሩክ ኮሚሽን ለሽያጭ ያቀረባቸው ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ መሆኑ ኮሚሽኑ ገለፀ፡፡ ሕዳር 14፣ 2016 ዓ.ም. (የገቢዎች ሚኒስቴር)

አንዳንድ ሚዲያዎች ሰሞኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ለሽያጭ ያቀረባቸው ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ህግን የተከተለ አለመሆኑን የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች የገለፁ መሆኑን በመጥቀስ የቀረቡት ዘገባዎች አግባብነት የሌላቸው እንደሆኑ ኮሚሽኑ ገለፀ፡፡
 
የጉምሩክ ኮሚሽን በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡ እቃዎች ላይ ቀረጥ እና ታክስ እንደሚሰበስብ የሚታወቅ ሲሆን ከጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ ጋር በተያያዘ ነባር ህግ ተቀይሮ ሌላ ህግ ሲወጣም አዲሱን ህግ የማስፈፀም ስራ የሚከናወን መሆኑ ይታወቃል፡፡
 
መንግስት ነባሩን የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ማለትም አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንዲሻር በማድረግ አዲስ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ማለትም አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ፀድቆ ተግባራዊ ያደረገ በመሆኑ እና በአዲሱ አዋጅ ከውጪ ምንዛሬ አጠቃቀም እና አካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ እንዲቀንስ እንዲሁም አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት የሚችሉበት ሁኔታን ለማበረታታት እንዲቻል ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የኤክሳይስ ታክስ ምጣኔ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡
 
አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡
 
በመሆኑም አሁን ጨረታ የወጣባቸው ተሽከርካሪዎች ከተጠቀሰው የመሸጋገሪያ ጊዜ ገደብ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ስለሆኑ በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ የተጠየቁ ቢሆንም በተሽከርካሪዎቹ ላይ የሚፈለገውን ቀረጥ እና ታክስ ከፍለው ተሽከርካሪዎቹን መረከብ አልቻሉም፡፡
 
በተጨማሪም ማንኛውም አካል ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያለው እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 153-155 ባሉ ድንጋጌዎች መሰረት በየደረጃው ለተቋቋመ የአቤቱታ አጣሪ እና ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እና መደበኛ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ መከራከር እንደሚችል በግልፅ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች መደበኛውን የአቤቱታ አቀራረብ ሂደት ወደ ጎን በመተው ተሽከርካሪዎቹ ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዝ ያመጡ ቢሆንም ኮሚሽኑ በተሽከርካሪዎቹ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ህግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዙን አንስተዋል፡፡
 
በዚሁ መሰረት ከተሽከርካሪዎቹ የሚፈለገውን የመንግስት ቀረጥና ታክስ አስመጪዎቹ ከፍለው መረከብ ባለመቻላቸው በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 1160/2012 መሰረት እንደተተወ እቃ ተቆጥረው በኮሚሽኑ የእቃ አወጋገድ መመሪያ መሰረት ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡
 
ስለሆነም ኮሚሽኑ በሽያጭ ለማስወገድ በይፋ ለጨረታ ያወጣቸው ተሽከርካሪዎች በህጉ መሰረት የተፈፀመ እንጂ አንዳንድ ሚድያዎች ግለሰቦችን ዋቢ አድርገው በዘገቡት የተዛባ መረጃ መሰረት አለመሆኑ ሊታወቅ የሚገባ እና ይህንን የአንድ ወገን መረጃ ብቻ በመውሰድ መዘገብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ታውቆ ሊታረም የሚገባ መሆኑን እና በቀጣይ መሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ የሚጠይቅ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.