በኮንትሮባንድ ዝውውር ተጠርጥረው የተያዙ 312 ግለሰቦች

Nested Applications

Asset Publisher

የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል

የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል Tue, 29 Oct 2024

የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ Tue, 29 Oct 2024

Asset Publisher

null በኮንትሮባንድ ዝውውር ተጠርጥረው የተያዙ 312 ግለሰቦች

በአራት ወራት 4.7 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሯ በአራት ወራት ከገቢ ኮንትሮባንድ 3.4 ቢሊየን ብር እንዲሁም ከወጪ ኮንትሮባንድ 1.3 ቢሊየን ብር በድምሩ 4.7 ቢሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ እቃዎችን መያዝ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

የታክስ አስተዳደሩን ኮንትሮባንድ፣ ደረሰኝ እና ህገ-ወጥ ንግድ እየፈተኑት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ በአራት ወራቱ አፈፃፀም በኮንትሮባድና ህገ-ወጥ ንግድ ተጠርጥርው ከተያዙ 312 ተጠርሪዎች ውስጥ በ258ቱ ላይ አስተማሪ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ አፈፃፀሙ በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ32.94 በመቶ ብልጫ ያለው አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም ኮንትሮባድና ህገ-ወጥ ንግድ ለህብረተሰቡ አስከፊነቱን የማስገንዘብ ስራዎች ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑን ገልፀው ለሕግ ተገዥ የማይሆኑትን ግን የታክስ ህጉ በሚፈቅደው ልክ እርምጃ እንደሚወሰድም አመላክተዋል፡፡

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.