በአራት ወራት 193 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል

Nested Applications

Asset Publisher

null በአራት ወራት 193 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል

የገቢዎች ሚኒስቴር ባሳለፍናቸው አራት ወራት ከ193 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ሊሰበስብ ካቀደው 196.36 ቢሊዮን ብር ውስጥ 193.98 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 98.78 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በ4 ወራት አፈፃጸም ከሀገር ውስጥ ገቢ 128.49 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ያቀደ ሲሆን 129.18 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 100.54 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ለመሰብሰብ ከታቀደው 67.88 ቢሊየን ብር ገቢ ውስጥ 64.79 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 95.46 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሯ በመግለጫው አንስተዋል፡፡

አፈጻፀሙ እንደ ተቋም ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የብር 30.99 ቢሊዮን ወይም የ19.02 በመቶ እድገት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ለተመዘገበው አፈፃጸም ውጤታማነትም በዋናነት በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና ሰራተኞች እየዳበረ የመጣው ጠንካራ የስራ ባህል መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል Tue, 29 Oct 2024
የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል
  • የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ Tue, 29 Oct 2024
የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.