የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ512 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል
መጋቢት 19/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የታክስ ሰርዓቱን ለማዘመን የወረቀት አሰራሮችን የሚያስቀር የኤሌክትሮኒክስ ኢንቮይስ ሲስተም አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ሰነድ ከከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ተፈራርሟል::
ስምምነቱን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሀሚድ ፈርመዋል::
በስምምነቱ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በህገ ወጥ ንግድ በቀረጥ እና ታክስ ማጭበርበር ምክንያት የኢትዮጽያ ኢኮኖሚ መሰብሰብ ያለበትን ገቢ ለመሰብሰብ አለመቻሉን አመላክተው ይህ ስርዓት የግብይት ደረሰኝን ከአንድ አካል ብቻ ማለትም ከገቢዎች ሚኒስቴር ብቻ እንዲቆረጥ በማድረግ በሃሰተኛ ደረሰኝ የሚደረግ ማጭበርበርን የሚያስቀር ነው ብለዋል::
ሚኒስትሯ ስርዓቱ ለነጋዴው ማሕበረሰብም ሆነ ለሸማቹ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረው የነጋዴው ማህበረሰብ ለደረሰኝ ሕትመት የሚያወጣውን ወጪና ጊዜ ከማስቀረቱም በላይ የግብይት ሂደቱን በቀጥታ ለመከታተልና ለመቆጣጠርም እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሀሚድ በበኩላቸው የሚዘረጋው የኤሌክትሮኒክስ ኢንቮይስ ሲስተም ስርዓት የማንዋል የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ወደኤሌክትሮኒክስ የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ለመቀየር የሚያስችል እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ስርአቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳልጥ መሆኑን አንስተው የሚዘረጋው ስርዓት ውጤታማ እንዲሆን የተቻለው ጥረት ሁሉ እንደሚደረግም ተናግረዋል::
ሐምሌ 21/ 2016 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡
በመድረኩ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 529.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ512 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ገልጸዋል፡፡
ከአምናው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ገቢው ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለውም ዘመናዊ እና ተደራሽ የታክስና የጉምሩክ አስተዳደር ስርዓትን በመገንባት አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረፅ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ በማድረግ የዕቅዱን ከ96 በመቶ በላይ እንዲሳካ አስችሏል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ህገወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ በሀገራዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ ገልፀው፤ በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ህጋዊነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ትብብር እንዲያደርጉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡