Asset Publisher

null በገቢዎች ሚኒስቴር በቀጣይ ለሚተገበረው የዲጂታላይዜሽን ውጥን የቅድመ ትግበራ ጥናት መካሄድ ጀመረ

ጥር 13፣ 2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የቅድመ ትግበራ ጥናት ሥራው በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኩል የፐብሊክ ዲጂታል ካምፓኒ ልኡካን አማካኝነት በዛሬው እለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የቅድመ ትግበራ ጥናት ሥራው በተመረጡ የስራ ክፍሎች ለ5 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል፡፡ በስተመጨረሻ በቅድም ትግበራ ጥናት ግኝት ዙሪያና በዲጂታላይዜሽን እሳቤ እንዲሁም ተግባር ዙሪያ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ሉዑካን ቡድኑን የተቋሙ ማኔጅመንት አባላት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ ለሚካሄደው የዲጂታላይዜሽን ተግባር የቅድመ ትግበራ ጥናት ስራው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ የፐብሊክ ዲጂታል ካምፓኒ ልኡካን ቡድን አባላት በሚኖራቸው ቆይታ ተቋሙ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አረጋግጠዋል፡፡

የልኡካን ቡድን አባላት በበኩላቸው፣ በተቋሙ በቀጣይ ለሚተገበረው የዲጅታላይዜሽን ተግባር አጋዥ የሆነ የቅድመ ትግበራ ጥናት እንደሚያከናውኑ ገልጸው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዲጅታላይዜሽን ውጥን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

የቅድመ ትግበራ ጥናት ሥራዉ በተቋሙ የስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ያስተባበረው ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ በቀጣይ ለሚያካሂደው ዲጂታል ትራንስፎሜሽን ዕቅድ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)